Sunday, May 8, 2016

ማስታወቂያ በህብረተሰቡ ዙሪያ

             
ማስታወቂያማለት ምርትና አገልግሎትን ማስተዋወቅ ነው። ይህም ማስታወቂያ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን እውቅና በጥቂቱ እገልፃለሁ ።

  ማስታወቂያ በህብረተሰቡ ዙሪያ ያለው እውቅና አብዛኛው የሕብረተሰባችን ክፍል ያልተማረና ስለ ማስታወቂያ በቂ ግንዘቤ ስለሌለው ማስታወቂያውን የሚሠማውም ሆነ የሚያቀርበው ክፍል ስለ ማስታወቂያ  በቂ የሆነ እውቀት የለውም ።ማስታወቂያውን የሚሰማው ህብረተሰብ ማስታወቂያ በሚሰማበት ጊዜ ሞንም አይነት ትችት እና ግምገማ ደካማና ጠንካራ ጎን ብሎ ለይቶ ስለማይገነዘቡት ማስታወቂያውን የተናገረውን ሰው መሰረት አድረገው ምርትናአገልግሎት ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ ።ማስታወቂያ ተናጋሪው ታዋቂ  ከሆነ የምርቱ ወይም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይጨምራል ።የማይታወቅ ከሆነ ደግሞ በአንፃሩ ይቀንሳል።

  ማስታወቂያን የሚያቀርበው ሞርቱናአገልግሎቱን የሚስተዋወቀው ያለ ምንም ህግና ደንብ ና በዘልማድ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ከዚህ ደርሷል ።አሁን ባለንበት ዘመን ግን ብዙም ባይባልም የተሻለ የማስታወቂያ እውቀትና ግንዘቤ አለው ።
     

 በአጠቃላይ ማስታወቂያው በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ግንዘቤ እና እውቀት ከላይ የቀረበውን ይመስላል ። በአሁኑ ዘመን ምርትና አገልግሎት ለለማስዋወቅ ማስታወቂያ የግድ ነው።

No comments:

Post a Comment