Wednesday, May 18, 2016

           
     የ"Axe" ማስታወቂያ ይዘት በኢትዮጵያ
 የ"axe" ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ሲተዋወቅ የጎደለው ነገር ምንድን ነው? በመጀመሪያ የማስታወቂያውን አቀራረብ ስንመለከት አንድ ወንድ ሲደመር አንድ "axe" ዶድራንት የምናገኘው አሉታዊ የሆነ ውጤት ማለትም አንድ ወንድና ሁለት ሴቶችን እናገኛለን። 
        
          ይህ ደግሞ የሴቶችን ከወንዶች ያላቸውን የእኩልነት መብትና ተገዥነታቸው ለወንዶች እንደሆኑ በግልፅ ያሳያል። ወንዶች ይህን ዶድራንት ሲጠቀሙ አበባ እንደምትቀዋ ንብ ተሰብስበው መጠው ወንዱን ሲከቡት ይስተዋላል። ይህ ማለት በዋናነት ማስታወቂያው ሲሰራ ምርቱ ለወንዶች ብቻ የሚያገለግል ሆኖ የቀረበና በአብዛኛው ለወጣት ወንዶች ብቻ የሚያገለግል ምርት እንደሆነ በግልፅ ያሳያል።
       
        ይህ አይነቱ የማስታወቂያ አቀራረብ ዘዴ ምርትን ወይም አገልግሎትን ለመሸጥ ሳይሆን ዝም ብሎ ብቻ ምርቱ ለገቢያ መቅረቡን ብቻ የሚያሳይ ነው። በዚህ ማስታወቂያ ሴቶችን የተጠቀሙባቸው እንደ ምርት አስተዋዋቂ ሳይሆን ለፆታዊ ስሜት ያላቸውን ድክመት የሚያሳይ ነው። ሴቶች በአጠቃላይ የ"axe"ን ዶድራንት የመግዛት አላማ አይኖራቸውም ምክኒያቱም ይህ ማስታወቂያ የሴቶችን ገላ ወይም ማንነት በምርቱ ወይም በአገልግሎቱ የመቀየርና ሴቶችን እንደ ቁሳቁስ የመቁጠር አላማ አለው።

          ማስታወቂያ ሲቀርብ በዋናነት የህብረተሰቡን ማንነት ባህል፣ቋንቋ፣አለባበስና ሌሎች ከህብረተሰቡ ጋር ተዛማጅ የሆኑማለም ሀይማኖታዊና ታሪካዊ ሂደቶች ላይ ተዛማጅነት ያለው ነገር ቢሆን ይመረጣል። ይህ ማስታወቂያ ከምስሉ በተጨማሪ ምንም አይነት የድምፅ ቅንብር የለውም። ይህ ማለት ያልተማረ ወይም ሌሎች ሰዎች ሊረዱት አይችሉም። በተጨማሪም ህብረተሰቡ በምርቱ ላይ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ ይሆናል። ማስታወቂያው በአጠቃላይ የሴቶችን የፆታ ፍላጎት በስሜታዊነትና ባለማስታዋል እንደሆነ የሚያሳይ ነው ።

No comments:

Post a Comment