Sunday, May 8, 2016

የማስታወቂያ ስርዓት

            
       የማስታወቂያ ሰርአት በኢትዮጵያ አብዛኛው ጊዜ የሚደመጡት የማስታወቂያን ስርዓት እና ደንብ ባልጠበቀ መንገድ በማስታወቂያ ተናጋሪው እና አስነጋሬው እንዲያመች ሆኖ የተዘጋጀ ነው።ማስታወቂያ ከጥንት ጀምሮ በዘፈቀደ የተነገረ ምርትና አገልግሎትሲያስተዋውቁበት ቆይቷል።

  በዚህ ማስታወቂያ ዘርፍ ህግና ደንብ ተቀርፆለት በስርዓት የተዘጋጀ አይደለም ።የማስታወቂያ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ አብዛኞውን ጊዜ ዝምብለው ያለምንም ህግና ደንብ በመሠላቸው መንገድ አስቀድመው አቀነባብረው ሲያቀርቡ ይስተዋላሉ ። 
    
 አሁን አሁን ግን ከጊዜ እናከስልጣኔ አንፃር ማስታወቂያ ዘመን ጠብቆ እድገቱ ብዙ ባይባልም ከበፊቱ የተሻለ ነው።    የማስታወቂያ በለሙያወች ፦የኢትዮጵያ የማስታወቂያ በለሙያወች አብዛኛውን ጊዜ በቂ የሆነ ትምህርታዊና ሙያዊ ስልጠና ስለማይሰጣቸው ማስታወቂያን በስርዓቱ አያዘጋጁም። እንዚህ በለሙያዎች እንደሌሎች ማህበራት ለምሳሌ ፦የጋዜጠኛ ፣የሲቢክናየመምህራን ማህበራት አንደሚባሉ የማስታወቂያ ማህበራት የሚባል የለም ።ይህም አንዱ የድክመት ማሳያ ነው።

     እነዚህ ከላይ የተመለከትናቸው ማስታወቂያ ችግሮች ጎልተው የሚታዪት በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻነው ።ማስታወቂያ በብዙሀንና በማህበራዊ ድረገጾች መተላለፍ ከጀመረበት ዘመን አንስቶ አሁን ከደረስንበት አለም ያለው የማስታወቂያ አሰራር በዘልማድ በሃላቀርነት እየቀረበ ይገኛል ።አሁን ግን ማስታወቂያወች እየተተቹ ስለሆነ ከበፊቱ የተሻለ አቀራረብና ስርዓት ባላቸው መልኩ የቀረበ ነው።

No comments:

Post a Comment