ማስታወቂያ በባህላዊ መንገድ
ሲተዋወቅ የማህበረሰቡን ባህል መሰረት አድርጎ ነወ ።
ሗላቀር በሆነ መንገድ ያለምንም የዘመናዊ መገናኛ መሳሪያዎችን ሳይጠቀም በቀጥታ በፈረስና በበቅሎ በየተጠቃሚዎች በር ለበር በማስተዋወቅ ምርትና አገልግሎትን ሲለዋወጡ ነበር
።
ማስታወቂያ በፈረስና በበቅሎ በቀጥታ ከድርጅቱ ወይም ካምራቹ
ምርትና አገለግሎትን በመውሰድ ለተገልጋዩ ወይም ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በቃላት
ድርደራ ብቻ በመሸጥ ተጠቃሚዎች ን ወይም ደንበኞችን ካምራች እና ከአገልግሎት ሰጪ አካላት ጋር በማስተሳሰር ትልቅ አስተዋጽኦ
እንደነበራቸው በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ የሚታወስ ነው
።
በዚያን ጊዜ የነበረው የማስታወቂያ
ስርአት በጣም አስቸጋሪና አሰልቺ
ከመሆኑ የተነሳ ምርትና አገልግሎትን ለተጠቃሚ ወይም ለተገልጋዩ
ለማሳወቅም ይሁን ባሉበት አገለግሎት ለመስጠት በጣም አድካሚ ነበረ
። ምክንያቱም ለብዙ ተጠቀሚዎች ምርትና አገለግሎትን ይጠቀሙ ዘንድ የማሳወቂያው ዘዴ እጅግ ሗላ ቀር ከመሆኑ የተነሳ ረጅም ጊዜንና ጉልበትን የሚጠይቅ ነበር ። ነገር ግን አሁን ባለንበት ዘመን በሀገራችን የተለያዩ ክፈሎች ምርትናአገለግሎትን ለተጠቃሚዎች
በቀላሉ ለማድረስ ያን ያህል ከባድ አይደለም ። ይህ የሆነበት ምክንያት
አሁን ላይ ብዙ የመገናኛ አውታሮች መኖራቸው ነው ።
ከላይ ያነሳሁአቸውን ሀሳቦች ተንተርሼ ከባህላዊ መንገድ ይልቅ በዘመናዊ መንገድ ምርትና አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ለማሳወቅ እጅግ
ጠቃሚውና ትርፋማ የሚያደረገው ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን ተጠቅመን መስራት ስንችል ነው የሚል
አመለካከት አለኝ ። እናም እንደ መፍትሔ ላነሳው የምፈልገው ነገር ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ አካላት ምርትና አገለግሎቱን ለተጠቃሚዎች በቀላሉ ለማሳወቅ ዘመናዊ የማስታወቂያ
ዘዴዎችን መጠቀም ቢችል የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ ።
No comments:
Post a Comment