አዝናኝና
አስቅኝ የቴሌቨዥን ማስታወቅያ
ማስታወቅያ በቴሌቨዥን ስናስነግር አብዛኛውን ግዜ በእጃችን የማይዳሰሰው ፣በምላሳችን የማንቀምሰው እንደሚቀመስና እንደሚዳሰሰ አድርገው በቴሌቨዥን ሲተዋወቅ እንመለከታለን ።ይህ
የማስታወቅያን ግነት ያመለክታል። ለምሳዔ የዱቄት ሳሙና ሲተዋወቅ ቀጥታ ቃሉን ከእንግሊዘኛ ከመውሰድ “ኦሞ” የሚለውን በመጠቀም
ሲሆን ልክ በምላሳችን እንደሚቀመስ አስመስለው ያቀርቡታል ።
ሌላው ደግሞ አስቂኝ የሆነ በምንም የማይገናኝ ማስታወቅያ ሲነገር ይሰተዋላል። ለምሳሌ በታለቁ የአበሐይ ህዳሴ ግድብ
ላይ በ8100A ላይ የገቢ ማሰባሰብያ ማስታወቅያ ሲሰራ በረከት ስለ
ግድቡ ሲያስተዋውቅ ምግብ እየበላ ነው። ይህ ዓይነት መስታወቅያ ደግሞ ሰዎችን በማስተዋወቅያው ግምት ከመስጠት ይልቅ እንደ ቀልድና
አስቅኝ እንዲመለከቱት ያደርጋቸዋል።
ከላይ የተመለከትናቸው ችግሮች በብዛት የሚከሰቱት የማስታወቅያ
ባለ ሙያ ነንለሚሉት ትልልቅን አዋቂ በሆኑ ሰዎች መካከል ነው። እነዚህሰዎች ምንም እንኳን በማስታወቅያ ስራን በርካታ ግዜ ቢቆዩም
ያለ ምንም ሙያዊ ስልጠናና ልምድ የላቸውም ። ይህም የማስታወቅያ
ዓይነት ተጠቃሚውን ከአምራቹ ጋራ እያራራቃቸው ይገኛል።
ይህ ማስታወቅያ በሕብረተሰቡ ላይ ያለው ተፅእኖ በርካታ
ነው። ከነዚህ መካከል ሰዎች ወይም ደንበኞች ለማስታወቅያው ያለውን ታማኝነትና ተጨባጭነት ያሳጣል።ባህልንና እውነታን እና ሌሎች ነገሮችን
ስለምያሳጣን ለሚነገረው ማስታወቅያን ትኩረት እንዲሰጥ ያደርገናል።
በአጠቃላይ የማስታወቅያ ስርዓት ጉድለቶች ለበርካታ ችግሮች ይጥላል። ይህም ችግር የሚከሰተው በሕብረተሰቡና በአምራች ድርጅት መካከል ይሆናል።
No comments:
Post a Comment