Sunday, May 8, 2016

የማስታወቂያ መተላለፊያ መንገዶች

         
       የማስታቂያ መተላለፊያ መንዶቾ በርካታ ናቸው ከነዚህም  መካከል  የልደትካርድ፣ የሠርግካርድ፣ፖስተሮች
የማስታወቂያ  ሠሌዳዎች ፣በኢንተርኔት ፣በሬድዮ፣በተሌቨዥን ወዘተ ይተላለፋል ።ከእነዚህ ከላይከዘረዘርናቸው መካከልሁሉምከህብረተሠቡአመችሆኖአይደርስም እነዚህን ዘዴዎች በሁለት አይነት መንገድ ከፍለን ማየት እንችላለን ።እነዚህም የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ማስታወቂያ ብለን እንከፍላቸዎለን።

 የህትመት ማስታወቂያ ፦ይህማስታወቂያ በብዛት ከህብረተሰቡ ጋር በፍጥነት የማይደርስ ሲሆን ያልተማረ ሰው በብዛት ሊጠቀምበት አይችልም ። ይህማስታወቂያ ጊዜ ፣ጉልበትንና ሐብትን ያባክናል ።ከነዚህም መካከል እነደምሣሌ የሚሆነን በራሬወረቀት ፣መፅሔት፣ ጋዜጣና የመሣሠሉትን መጥቀስ ይቻላል ።
  
  የኤሌክትሮኒክስ ማስታወቂያ ፦ይሕ ማስታወቂያ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች በመጠቀም ማስታወቂያን ወይም መልዕክትን የምናስተላልፍበት መንገድ ነው። ኤሌክትሮኒክስ ማስታወቂያ ፈጣንና ቀልጣፋ ስለሆነ ማንኛውም ሠው ሊመለከተው ወይም ሊሠማው የሚችል ነው።ይህም ማስታወቂያ ጊዜን ፣ጉልበትናሐብትን ይቆጥባል።ለምሳሌ ሬድዮ ፣ኢንተርኔት እንደ ምሳሌነት መጥቀስ እንችላለን ።
  

  በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው ጠቀሜታና ጉዳትም አላቸው ለምሳሌ የሕትመት ማስታወቂያ ጊዜን ገንዘብንያባክናል ።ከሕብረተሠቡ ዘንድ በተፈለገው ጊዜ በትክክል አይደርስም ።ኤሌክትሮኒክስ ማስታወቂያ ደግሞ የመሬት አቀማመጥ ፣መሠረታዊ ልማቶች ፣ያልተማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ሌሎች ነገሮች ተፅዕኖ ያሳድሩበታል።

No comments:

Post a Comment