በቴሌቨዥን የምንመለከታቸው ማስታዎቂያዎች በአብዛኛው ጊዜ የሚኬርቡበት
ሁኔታ በጣም ዝቅ ያለና የተመልካችን ስሜት መቆጣጠር የችሰችል ነው። አንዳንዶቹ በድብቅ እንደ ሬዲዮ ድምፅ ብቻ ሰምተን ያለምንም
ምስል ሲተዋወቁ እንመለከታለን ይህ ዋናው ችግሩ ነው። ሌላው የቴሌቪዥን ችግር ደግሞ የጊዜ ቆይታውና የአተር ሰአቱ አመቺ አለመሆኑ
ነው ።
የቴሌቪዥን ማስታዎቂያዎች በደንብ ቢሰራባቸ ህብረተሰቡን ወይም ደንበኛን
በቀላሉ የማሳመን ብቃት አላቸው ይህ የሆነበት ምክኒያት በምስል የተደገፈና በቀላሉ አስተዋዋቂው ከሚናገረው ቃላት በላይ የምስሉ አሳማኝነት ከመጠን በላይ ነው። ማስታዎቂያዎች አብዛኛውን ጊዜ ሲተዋወቁ
ለሬዲዮና ለቴሌቪዥን ተብሎ ስለማይዘጋጁ ለአድማጭ ወይም ለተመልካች ብዥታን ሲፈጥሩ ይስተዋለወል።
ሰዎችን ማሳመንና ምርትን ወይም አገልግሎት በአጭር ሰአት ለመሸጥ
ከተፈለገ ማስታዎቂያችንን የምናስተላልፍበት መንገድ መለየት አለበት ምክኒያቱም መገናኛ ለሰው ልጅ ትልቅ ሀይለ አለው በሬዲዮ የሚተላለፉ
ማስታዎቂያዎች ምስል አልባ ስለሆኑ ከፍተኛ አሳማኝ ቃላትን እንጠቀማለን ማስታወቂያን በአብዛኛው በአንድ በሁለትና ከዚያ በላይ ቤሆኑ
ሰዎች ይቀርባል ።
ሌላው
ደግሞ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ነው ይህ ማስታዎቂያ በምስልና በድምጽ እየተቀነባበረ ስለሆነ ሰዎችንየማሳመን ሀይል አለው። ምስሉ ለሰዎች
የሚፈጥረው እውቅና የአሰራር ሂደቱና ማስጠንቀቂያ የሆኑ ነገሮች በግልጽ ይታያሉ የምርቱ ወይም የአገልግሎት ጠቀሜታና ጉዳት በግልጽ
ይታያሉ። በአጠቃላይ የምናስተዋውቀውን ማስታወቂያ በምንና እንዴት እንደምናስተዋውቅ ማወቅ ይኖርብናል ማለት ነው።
No comments:
Post a Comment